ስለ እኛ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማዋቀር ባወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 ከተዋቀሩ አስፈፃሚ አካላት አንዱ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ነው፡፡
መስሪያ ቤቱ በከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ የመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት ወጥና ስታንዳርዱን የጠበቀ፣ ደህንነታቸው የጠበቀ ፣ፅዱና ምቹ የሆነ ምድረ ግቢ ያላቸው ህንፃዎችን በማልማት ቀልጣፋና ውጤታማ የአሰራር ስርዓት እንዲኖር የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ከብክነት የፀዳ የንብረት አስተዳደር ስርዓት ማስፈን ነው፡፡
ተግባርና ኃላፊነት
የቴክኒክ ድጋፍ
በመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ላይ ለከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ ያማክራል፤
የንብረት ምዝገባ
የከተማውን አስተዳደር ህንፃዎችንና ቋሚ ንብረቶችን ይመዘግባል፤ በበላይነት ያስተዳድራል፤ ያድሳል፤
መዋቅር ዝርጋታ
የህንጻና ንብረት አስተዳደር እና አጠቃቀም ዘመናዊ ስርዓትን ይዘረጋል፤ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ያረጋግጣል።
ውጤታማነት
የመንግስት ህንፃዎች አጠቃቀም፣ ለተጠቃሚው ያላቸው ተደራሽነት እና ከወጪ አንፃር ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
የንብረት ኦዲት
በመንግስት የንብረት አያያዝ ስርዓት መሰረት የመንግስት ንብረቶች በአግባቡ ስለመያዛቸው እና ጥቅም ላይ ስለመዋላቸው ኦዲት ያደርጋል።
የህግ ቁጥጥር
በባለስልጣኑ በሚያስተዳድራቸው ንብረቶች ላይ የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶችን ይከላከላል፤ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል።
አድራሻ
የቢሮ አድራሻ
ፒያሳ እሳት አደጋ ስራ አመራር ፊት ለፊት አበባዬ/ራህመት ታቦር ህንፃ 5ኛ ወለል
ስልክ
0114705811
Addis Ababa Public Property Authority
Telegram
@ppaacom1